Books, Book reviews, Film reviews
Short stories, and more

STIFHAB

BOOKS AND FILMS

             ፊልም   ባለ ታክሲው 
         
          ዳሬክተር      ዮናስ ብርሃን መዋ
         ገምጋሚ  
 
አንድ የፊልም ሥራ የማን ነው? ወይም ስለማን ነው? ብሎ መጠየቅ የተለመደ አይደለም ፡፡ በአንፃሩ ፊልሙ ስለምንድን ነው  ተብሎ ነው የሚጠየቅ ፡፡ ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡ አንድ ፊልም ለዚህ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ  መስጠት ካልቻለ ታሪኩ አንድ ከባድ ችግር አለበት ማለት ነው፡፡

  ባለታክሲው ስለምንድ ነው? 
ባለታክሲው - የአንድ ትልቅ ድርጅት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ በአጋጣሚ አይቶ የወደዳትን ውብ ወይዘሮ ለማጥመድ ታክሲ ነጂ መስሎ ስለሚያደርገው ክትትል ነው፣  ብለን በአጭሩ ማስቀመጥ እንችላለን፡፡ የታሪኩ ዋና መስመር ይኸው ነው፡፡ ይህ ነው የታሪኩ አከርካሪ the spine of the story (story line) የሚባለው፡፡ ስለሆነም የፊልሙ ትይንቶች ሁሉ በዚህ አከርካሪ ዙሪያ ማጠንጠን አለባቸው፡፡

     ዮናስ (ዋናው ገፀ ባህሪ) በሜሮን ባህሪና ውበት ተነድፏል ፡፡አላማው እስዋን ማግኘት ነው እሱዋን ለማግኘት የሚከፈለውን መስዋዕትነት በሙሉ ለመክፈል ዝግጁ ነው፡፡  ፊልሙ ባለታክሲው ስለምንድነው ለሚለው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ከመሰጠቱም በላይ ታሪኩ ጥርት ያለ ግብ (motivation) ያለው ሆኖ ይገኛል:: ዋናው ገፀባህሪ ወደዚህ ግብ የሚያደርገውን ጉዞና የሚገጥመውን እንቅፋት፡ እንቅፋቱን ለማለፍ የሚወስደውን ርምጃ፡ በመካያው የሚደርስበትን የማይፈታ መሳይ ችግር እያሳየ ጡዘቱ ላይ መድረስና ከዚያም ዋናው ተሳክቶለት አላማው ላይ መድረሱን ወይም አለመድረሱን በማሳየት መጠናቀቅ አለበት .............

ሙሉውን ለማንብብ እዚህ ይጫኑ፣   ባለ ታክሲ

Click here to read review ፍቅር ሲፈርድ

ፍቅር ሲፈርድ


ፍቅር ሲፈርድ -ሲፈረድበት / በፓስወርድ

ፊልም -የቴድሮስ ተሾመ ፍቅር ሲፈርድ

ዳይሬክተር - ቴድሮስ ተሾመ
ደረሲ - ቴድሮስ ተሾመ

                    ፊልም መስራት እንጂ ፊልም ማየት ለኢትዮጵያዊያን አዲስ ነገር አይደለም። በኢትዮጵያ፥ ፊልሞች ከግማሽ ምዕት ዓመት ላላነሰ ጊዜ ሲታዩ ቆይቶኣል። አሜሪካን የታየ ፊልም ብዙ ሳይቆይ ኢትዮጵያ ውስጥ ይታያል። በዚህ የተነሳ ኢትዮጵያዊ ሲኒማ ሃጅ የዓለምን የፊልም ደረጃ ብቻ ሳይሆን የፊልሞችን ዣነር ወይም ዘውግ ጭምር መረዳት አያቅተውም። ለምሳሌ የዴራኩላ ሆረር ፊልም ውስጥ ቀን እንደ ሰው በሁለት እግሩ ሲዳክር የሚውለውን ፍጥረት፥ ጨለምለም ሲል እንደ አሞራ ክንፍ አውጥቶ ሲበር ቢያየ አይደነቅም። ተኣመኒነቱንም አይጠይቅም። ምክንያቱም በዚያ ዣነር ውስጥ የተመደበ ፊልም ስናይ እንዲያ ዓይነት ነገሮችን እንዲከሰቱ በተለምዶ እናውቃለንና።

ሳይንስ ፊክሽን ስናይ፣ ለዚህ ለገሃዱ እውነታ ተዐምር የሆኑ ትይንቶች እናስተውላለን። በጊዜ ወደ ሁዋላ መጉዋዝና ቅድመ አያትን አዋልዶ መመለስ ወይም ወደፊት ተጉዞ ልጅ ሳትወልድ የልጅ ልጅህ ሰርግ ላይ መገኘትን እንቀበላለን። በእወነታ ላይ የተመሰረተ ወቅተዊ ፊልም ስናይ ግን የማህበራዊ ኑሮ ደንብና ልማድን የሚያፋልስ ትይንት ስናይ ለመቀበል ከመቸገራቸን ባሻገር ፊልሙን አይቶ ለመጨረስም ትእግስታቸን ይሙዋጠጣል።

ፍቅር ሲፈርድ እውነታ ላይ የተመሰረተ ወቅታዊ የፍቅር ፊልም እንድመሆኑ መጠን ትይንቶች በሙሉ ከሞላ ጎድል ተዓመኒ እንዲሆኑ የግድ ነው። የገጸባህሪያት ተገባር፣ የነገሮች መንስኤና የችግሮች መፍትሄ አሳማኝና ግልጽ መሆን አለባቸው። ገጸባህሪያት ከተሳሉና በተሰጣቸው መቸት ወስጥ መንቀሰቀስ ከጀምሩ በሁዋላ ደረሲው የፈለገውን የማድረግ መብቱ በጣም ውሱን ነው።

ሙሉውን ለማንብብ እዚህ ይጫኑ; ፍቅር ሲፈርድ

Welcome

Recent Blog Entries

Newest Members

Donate!

  • No current campaigns

Recent Forum Posts

Oops! This site has expired.

If you are the site owner, please renew your premium subscription or contact support.