STIFHAB

BOOKS AND FILMS

Welcome to Stifhab 

ወደ ድረገጽ ጣቢያችን እንኳን ደህና መጡ። 
የተለያዩ መጻሕፍት፥ ልም ስክሪፕቶችና የመሳሰሉትን በነጻ ለማውረድ በክለብ  ኣባልነት  ይመዝገቡ።


[email protected]                                      
[email protected]
 Book reviews, film reviews, screenplays and more.

ስቲፍሃብ 

የመጽሐፍና የፊልም ክበብ


ስቲፍሃብ ከፖለቲካና ከሃይማኖት ነፃ የሆነ የጥበብ ክበብ ነው። ዓላማችን በሥነጽሁፍና ፊልም ሥራዎች ዙሪያ መሰባሰብ፥ መወያየትና መተጋገዝ ነው። ሌላ ዓላማ የለንም። የቀለምና የቋንቋ ልዩነትም ኣናውቅም። ስለሆነም በህገ ክበባችንን የሚስማማ ጥበብ ኣፍቃሪ ሁሉ አባል መሆን ይችላል። ታሪክን በልቦለድ

ታሪክን ማወቅ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆን እየገባኝ የመጣው አሁን አሁን ነው፣ የ'ያለማወቅን' ጉዳት ማየት ስጀምር። በአገራችን የትምህርት ካሪኩለም፥ የኢትዮጵያ ታሪክ፥ እንደ አንድ 'ሰብጀክት' የት/ ዓይነት፥ ወይም ከመደበኛው የታሪክ ትምህርት ውስጥ ተቀላቅሎ እንኳን፥ ስለማይሰጥ፥ እንደኔ የአገራችንን ታሪክ ሳያውቅ ሁለተኛ ደርጃ ትምህርቱ አጠናቅቆ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ስራ አለም የገባው ሰው ብዛት በሚሊዮን ይቆጠራል ብዬ እገምታለሁ። የአገሪቱ ታላላቅ ቅርሶችና እሴቶች፣ የህዝቧን አመጣጥና አሰፋፈር፣ ስለየብሄሬሰቡ ባህልና ቁዋንቁዋ፥ ስለ ቅርሶቻችን፥ በታሪክ አጋጣሚ የተካሄዱት የርስ በርስ ውጊያ መንስዔ፥ ወዘተ. . . ምናልባት በግሉ ያነበብ ካልሆነ በኔ የወጣትነትና የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤት የተማረው ሰው መኖሩን ኣላውቅም። ሰፊው የቀድሞው' the march of time, the old world የሚባሉ የኣውሮፓ መጻህፍት ይሸመድድ እንደነበር ኣስታውሳለሁ። የግብጥን ፒራሚድ አንጂ ስለ ኣክሱም ሃውልት ኣልተማርንም።  ለዚህ ነው፥ ~የኣክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነው?~ የሚሉን። 
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘውድ ከጫኑበት ጊዜ ወዲህ ስላለው ዘመናይ ታሪክ እንኩዋ በውል የምናውቅ ብዙዎች አይደለንም። ይህ ሁኔታ በእጅጉ አስከፍሎናል ብዬ አምናለሁ። በኛ ትውልድ ላይ አሁን የሚታየው የአለመግባባትና የመወነጃጀል፣ የትንንቅና የመጠፋፋት ችግር አንዱ ምክንያ ይኽው ታሪክን በቅጡ አለማወቃችን እንድሚሆን የሚያጠራጥር አይመስለኝም።

የጠላትን ወረራ ዐላማ በውል ብናውቅ ናሮ ዛሬ የነጻነትን ትርጉሙ እንደማያውቅ ህዝብ አገራችን በነጻ አውጭ ድርጅቶች ባልተጥለቀለቀች ነበር። በገዛ አገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠር ማለት ምን እንደሆን  የደረሰባቸው ቢተርኩልን ኖር፣ ዛሬ ኢትዮጵያ ቅኝ ገዛችን የሚሉ ጉዶች ባላየን ነበር። ጠላት የተቆጣጠራቸውን ግዛቶች ያሰተዳድር በነበረ ጊዜ በየቤቱ ይፈጸምው የነበረው ኣሰቃቂ ግፍ ቢነገረን ኖሮ፣ ዛሬ አይ ጣሊያን ትንሽ ቢገዛን የሚል ቀልደኛ ባልሰማን ነበረ። ስለ ሃገራችን ጀግኖች ተምረን ቢሆን ኖሮ፣ ፋኖ ተሰማራ፣ እንደ ሆቺሚን እንደቸጉቬራ እያልን ባላቅራራን ነበር። የፊደላችንን አፈጣጠር፣ ትርጉምና እሴት ፊደሎቹን ስንቆጥር ጀምሮ ብንማር፣ አፍሪካ ውስጥ የራሳችን ፊደል ያለን ህዝብ መሆናችን ያኔ ቢነገረን፣ ዛሬ ያን ክብር የሚሽጥ ዜጋ በልተፈጠረብን ነበር። ሃይማኖታችንም ያው ነው። ዘመን አመጣሽ እምነቶችን በቀላሉ ተቀብለን የራሳችንን የምናኳስሰው  የነበሩንን አገር በቀል፥ ያሉንን ጥንታዊ ሃይማኖቶች ኣመጣጥና ለሀገር ነፃነትና ህልውና  የከፈሉትን መስዋዕት ካለመገንዘባንች የተነሳ ሊሆን አንደሚችል ብዙ ኣልጠራጠርም። 

የአለማወቃችን ጦስ ብዙ ነው፣ በክብር፣ በንብረት፣ በጊዜና በህይወት ከፍለንበታል። አሁን ድረስም እየከፈልንበት ነው። ታሪካችንን ካላወቅን ወደፊትም በውድ መክፈላችን  እንቀጥላለል። ይህን ሁኔታ የምንቀይረው በእውቀት ብቻ ነው። እውቀት ትክክለኛውን ግንዛቤ እንድንይዝ፣ የችግሮቻችን መንስዔ እንድናውቅና ትክክለኛ መፍትሄ እንድናገኝ ይረዳናል። ውሽትን ከእውነት፣ ያለተደረገውን ከተደረገው የምንለየው ስናውቅ ነው። ፖለቲክኞች ለራሳቸው ዓላማ የፈጠሩትን ታሪክ ከእውነተኛው ታሪክ መለየት የምንችለው እውነተኛውን ታሪክ ስናውቅ ብቻ ነው። አልያ አሉባልታን እንደ ታሪክ ወስደን ያልሆነ መደመደሚያ ላይ ከማረፍ አልፈን የማያስፈልግ መስዋእትነት እስከመክፈል እንደርሳለን።

ታዲያ ታሪክን በትምህርት ቤት ካልተማርን ከየት መማር እንችላለን?

ታሪክን ከተለያዩ የታሪክ መጻህፍት መማር ይቻላል። ስለሃገራችን ታሪክ በቁዋንቁዋችንም ሆነ በውጭ ቁዋንቁዋ የተጻፉ መጻህፍት አይጠፉም። እነዚያን መጸህፍት በመመርመር ታሪክ ማወቅ ይቻላል። እንዲ ያሉ መጸህፍትን ግን አሳድዶ የማንበቡ ተነሳሽነት የሚታየው በአብዛኛው በሙያው ሰዎች ወይም በጉዳዩ ልዩ ጥናት በሚያደርጉ ሰዎች እንጂ ሌላው  ደረቅ ታሪክን ቁጭ ብሎ የማንበብ ትእግስት የለውም። የደረቅ ታሪክ አጻጸፍ ስልት አጉዋጊና መሳጭ ስላልሆነ ልዩ ዝንባሌ የሌለውን ሰው የመያዝ ኃይሉ እስከዚህም ነው። በትምህርት ቤትም ብዙዎቻችን የታሪክ መጻህፍት የምናጠናው ፈተናውን ለማለፍ እንጂ ታሪኩን የማወቅ ፍላጎት ወጥሮ ስለሚይዘን አይደለም።

አንባቢን ቴሌቪዥንና ፊልም ከመሳሰሉ አዝናኝ የጥበብ ዘርፎች ስቦ የታሪክ መጽሃፍ እንዲያነብ መጽሃፉ በእጅጉ መሳጭና ስሜት ኮርኩዋሪ በሆነ ስልት መጻፍ ይኖርበታል። የልቦለድ አጻጻፍ ስልት እይታችን ውስጥ የሚገባው እዚህ ላይ ነው። ታሪክ በልቦለድ አጸጻፍ ስልት ሲጻፍ ታሪካዊ ልቦለድ ይባላል። የታሪካዊ ልቦለድ አጻጸፍ ስልት መቸቱን፣ ገጸባህሪያትን፣ የታሪኩን መንስኤ፣ ሂደቱንና ፍጻሜውን የሚያቀርብበት ልዩ ዘዴ አለው። ደረሲው እኒያን ዘዴዎች በመጠቀም ማሳወቅ የፈለገውን እውነተኛ ታሪክ በልቦለድ አለባብሶ ያስተላልፋል። የሚጎመዝዝ መድሃኒት በማር ጠቅልለው እንደሚያስውጡን፣ አሰልቺውን ደርቅ ታሪክ በልቦለድ አጣፍጠው ያስነብቡናል።  

    ዘርዓይ ደረስ የፋሽስቶችን አንገት በጎራዴ መቅላቱን በቀር ውስጠ ጉዳዩን ጠልቄ የተረዳሁት በታሪካዊ ልቦለድ መጽሀፍ ነው። ስለ አምስቱ ዐመት የጠላት ወረራ ዘመን ያለኝ ግንዛቤ በሰፊው ያገኘሁት ታሪክ ቀመስ ከሆኑ ልቦለድ መጻህፍት ነው።  የእስረኤልና የፍልስጤምን መሰረታዊ ችግር በመጠኑ የተረዳሁት "ኤክሶደስ" ከተሰኘው ታሪከዊ ልቦለድ ነው። ታሪካዊ ልቦለድ ታሪክ የማስተማሪያ አንዱ መንገድ ሊሆን ይችላል የምለው ለዚህ ነው።

እና እናንብብ።                  መኮንን ገ/እግዚ